Wednesday, November 20, 2019

የነፍስ ተማፅኖ

መልካሙ እረኛ ዳዊት ከወዴት አለህ???
ንጉሡ ሳኦል እስራኤላውያንን ከመከራ ሊታደጋቸው እንዳልቻለ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ፊቱ ወደ እሴይ ቤት መለሰ በዚያም ትንሹን የበጎቹን ጠባቂ አንበሳን በጡጫ ነብርን በቡጥጫ የአራዊትን አንገት እያነቀ በጎቹን ከአውሬ የሚጠብቀውን እንደልቤ ያለውን ብላቴና ዳዊትን ተመለከተ ። ሳሙኤልንም አለው ተነስ ወደ እሴይ ቤት ውጣ ከልጆቹም አንዱን ቀብተህ አንግስ ቢለው ሳሙኤልም ቅበዐ ንጉሱን ይዞ ወደ እሴይ ቤት አመራ በቤቱም እንደደረሰ እሴይ ወዳጄ ሆይ!!!!  እግዚአብሔር በቤትህ ልኮኛልና ልጆችህን ጥራ ፈጣሪ ከልጆችህ አንዱን እቀባ ዘንድ አዘዘኝ!! ሲለው እሴይም ከልጆቹ መሃል መልከ መልካሞቹን እነ ኤልያብን ቁመተ ሎጋወቹን አፍንጫ ሰልካካወቹን ትከሻ ደልዳላወችን አንደበተ መልካሞቹን እየመረጠ ወደ ሳሙኤል ቢያቀርብም እሴይ እንጅ እግዚአብሔር አልመረጣቸውምና ቅብዐ ሜሮኑ ፀጥ አለ ሳሙኤልም ወዳጄ እሴይ ሌላ ልጅ የለህምን ?  ሲለው ጠየቀቀ  አይይይ ለንግስና የሚሆን የለኝም አንድ የበጎች ጠባቂ አለ እሱ አይሆንም ቢለው ሳሙኤልም እረኛውን ጥሩልኝ አለ ፤ ከሚጠብቅበትም ጫካ ዳዊት ተጠራ የበጎቹ እረኛ ገና ወደ ሳሙኤል ከመድረሱ ቅበዐ መንግስቱ በቀንዱ ላይ ሽቅብ መፍላት በጀመረ ጊዜ እግዚአብሔር የመረጠው ልጅህ እነሆ ብሎ ቅብዐ መንግስቱን በራሱ ላይ አፈሰሰ ......የበጎቹ እረኛ የተናቀው ብለቴናው ዳዊት ወንጭፉን አንስቶ እስራኤላውያንን ከመከራ ፣ ከጎልያድ ገላገላቸው እረፍታቸውንም አገኙ ።
እነሆ የበጎቹ እረኛ ዳዊት ሆይ ከወዴት አለህ ??????